ችግር ፈቺ ምርምሮች እና ገቢ ማመንጨት ላይ ያውጠንጠኑ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል

ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የተቋማችን ተመራማሪዎች በነገው ዕለት ፕሮጀክት ፕሮፖዛላቸውን አቅርበው በሰራተኛና አመራሮች
ፊት ያስገመግማሉ፡፡ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ ችግር ፈቺ ምርምር እና ገቢ ማመንጨት ላይ እንደሚያውጠነጥኑ የሚጠበቁት እነዚህ
ፕሮጀክቶች በኢንስቲትዩቱ የስብሰባ አዳራሽ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ‘‘Digitizing Finance: Mobile Payment’’ በሚል ርዕስ የአንድ ቀን ወርክሾፕ በስብሰባ አዳራሻችን አዘጋጅቷል

ዳር 24 2012 (Dec 4) የአንድ ቀን ወርክሾፕ በስብሰባ አዳራሻችን አዘጋጅቷል፡፡ ፡፡ በዚህ ወርክሾፕ መሳተፍ ለምትፈልጉ
ሁሉ በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት እስከ ሰኞ ህዳር 22 ድረስ ብቻ መመዝገብ ትችላላችሁ
https://docs.google.com/…/1FAIpQLSfYpO3jXQj8vTabRM…/viewform
ለተመራጭ ተሳታፊዎች ውጤቱን በኢሜይል የምናሳውቅ ሲሆን ተጨማሪ ጥያቄ ካልዎት በኢሜይል አድራሻችን
conference@techin.gov.et ያድርሱን፡፡

ያለን ቦታ አነስተኛ ነውና ይፍጠኑ!!!

የTECHIN ቤተሰቦች የክህሎት ግንባታ

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መመስረቱን ተከትሎ ተቋሙን ለተቀላቀሉት ባልደረቦቹ የእርስ በእርስ ትውውቅ እና ክህሎትን
ለማዳበር ያለመ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ዛሬ ጅማሬውን አድርጎ ለተከታታይ ፲ ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ በተለያዩ ተቋማት እና ኃላፊነቶች እያገለገሉ የሚገኙ
ምሁራን እና ባለ ታላቅ ስብዕና ግለሰቦች ልምዳቸውን ለተቋሙ ሰራተኞች እንደሚያካፍሉ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በተለያዩ
መድረኮች በምትሰነዝራቸው አስተያየቶች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ስራዎቿ እውቅናን ያተረፈችው ሎሬት
የትነበርሽ ንጉሴ፣ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ይጠቀሳሉ፡፡

በዛሬው መርሀግብር ላይ በemotional intelligence ዙሪያ የስነ ልቦና አማካሪ በሆኑት ወይዘሮ ሰብለ ኃይሉ አማካኝነት
ለአንድ ቀን የቆየ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

የሰመር ካምፕ ተወዳዳሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸው

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ያዘጋጀው እና ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ሲካሄድ
የቆየው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በእውቅና እና የሽልማት ስነ ስርዓቶች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ የሰመር ካምፕ
ፕሮግራሙ በዋናነት የመንግስት ተቋማት የአሰራር ስርዓትን የሚያዘምኑ የሶፍትዌር ፕሮጀክቶች ማበልጸግ እና ማቅረብ በሚለው
የትግበራ ዘርፍ ላይ አተኩሮ የተሰናደ ሲሆን፣ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ አመልካቾችም በመነሻነት መሳተፋቸውን በስነ ስርዓቱ ላይ
ተጠቅሷል፡፡

ወደ ሃብት ሊቀየሩ የሚችሉ ግዙፍ መረጃዎች ቢኖሩንም አልተጠቀምንባቸውም

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት ከዜናይሲስ (ZENYSIS) ቴክኖሎጂስ ጋር በትብብር ያዘጋጀው እና ዋና ትኩረቱን በግዙፍ
የመረጃ ትንተና (big data analysis) እና አድቫንስድ ኮምፒዊቲንግ (advanced copmputing) ላይ አድርጎ
የተሰናዳው ወርክሾፕ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች
የተሳተፉ ሲሆን ጥናትና ምርምሮችን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያከናወኑ ምሁራንም ተሳትፈውበታል፡፡

በፕሮግራሙ መጀመሪያ ላይ የመክፈቻና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ
ሃገራችን ሌላው ዓለም እየሄደበት ያለውን የመረጃ እና ቴክኖሎጂ ግስጋሴ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን አድራጊ እና ፈጣሪ ልትሆን ቢገባትም
የመረጃን ወሳኝነት በሚገባ ካለመረዳታችን እና ካለመገንዘባችን የተነሳ ብዙ ወደ ውጤት ልንቀይራቸው የሚገቡ ሃብቶች ሳንጠቀምባቸው
እንደቀሩ አንስተዋል፡፡ መረጃ የቀጣዪ ጊዜ ወርቅ እና ነዳጅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት
ይህንን መሰረታዊ ሃቅ በመረዳት በግዙፍ የመረጃ ትንተና እና አድቫንስድ ኮምፒውቲንግ ላይ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን
ጠቁመዋል፡፡

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከIBA ኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

ጀማሪ ፈጣሪና ቴክኖሎጂስቶችን በማብቃት ላይ የሚሰራው IBA ኢትዮጵያ በቴክኖጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በመገኘት በጋራ
መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ውይይትን አድርጓል፡፡ በአርባ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የኢኖቬሽን
ማዕከላትን በማቋቋምና ያሉትንም በመጠናከር ዙሪያ ሊሰሩ ያቀዱትን ጨምሮ በኢትዮጵያ እንዲሁም በኖርዌይ እየሰራቸው ባለባቸው
ተግባራት ዙሪያ ተቋሙን ወክለው የመጡት ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከኢንስቲትዩቱም የሰው ኃይል እና መሰረተ ልማት ድጋፍን
እንደሚሹ አስቀምጠዋል፡፡

የቴክሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ከIBA ጋራ ሊሰራባቸው በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ
ገለፃን የሰጡ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ማቅረብ የሚችለውን የሰው እና የቁሳቁስ ሐብት በመጥቀስ ለሐሳቡ ያላቸውን ቀናዕይነት
ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ ከገለፃቸውም ዘርፎችም በተጨማሪ በሀገራችን ለውጥ በሚያመጡ መሰረታዊ ቴክኖሎጂዎች ላይም ትኩረቱን
እንዲለግስ ጠይቀዋል፡፡