...

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን ሰርቶ አቅርቧል

በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲቱዩት በምርምርና ልማት ዳይሬክቶሬቱ አማካኝነት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከጥጥ ጨርቅ (Cotton fabric) የተሰራ የፊት መሸፈኛ ጭምብል (Face mask) አምርቷል። ጭምብሎቹ በሁለት ዲዛይን ሲሰሩ የመጀመሪያው የአይን መሸፈኛ ያለው (with eye shield) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የሌለው ነው፡፡

ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች እና ለአከባቢው ማህበረሰብ የሚሰጡት እነዚህ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች በሀገር ዉስጥ የጥጥ ጨርቅ የተሰሩና ታጥበውዳግም ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሲሆኑ ከጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጋራ በትብብር የተሰሩ ናቸው።

የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከዚህ በተጨማሪም ባለንበት የኮሮና ወረርሺኝ ወቅት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ከዚህ ቀደምም የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን የተመለከቱ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች የሚስተናገዱበት የማዕድ ማጋራት ፖርታል እንዲሁም የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን በራሱ ተመራማሪዎች አሰርቶ ለህዝብ እና የተቋሙ ሰራተኞች ማቅረቡም ይታወሳል፡፡Post Comments(1)

...
dobson1 day, 21 hours ago

4rh1qO buy cheap cialis http://pills2sale.com/

Leave a reply