...

አዲሱን የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳን አስመልክቶ የተደረገው ምክክር

ለአዲሱ ፖሊሲ ክለሳ ግብዓት ይሆን ዘንድ ዛሬ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተካሄደው ምክክሩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ተሳታፊዎችን ተሳታፊ ያደረገ ነበር፡፡ በምክክሩ ላይ በሚኒስቴሩ የፖሊሲና ፊውቸር ፕላኒንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደስታ አበራ ቀድሞ በስራ ላይ ስለነበረው እንዲሁም ክለሳ ተደጎበት በመጣው ፖሊሲ ላይ ዝርዝር ማብራርያ ለታዳሚያኑ አቅርበዋል፡፡ የቀድሞው ፖሊሲ ችግሮች ቢኖሩበትም ምጣኔ-ሐብታዊ ዕድገት ማስመዝቡን የገለፁት አቶ ደስታ አጋጠሙት የተባሉት ተግዳሮቶችን በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡ ለአዲሱ ፖሊሲ ክለሳ መነሻ ሁኔታዎች ሆነው የተቀመጡትን ጉዳዮች እንዲሁም ክለሳው ሲሰራ የተከተላቸው ፍልስፍናዎች በአቶ ደስታ ገለፃ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል፡፡

የፖሊሲ ክለሳው ታድያ በዋናነት ተግባር ላይ የቆየውን ፖሊሲ ድክመቶች በማሻሻል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እኛም 2012 እና በያዝነው ዓመት ታትመው ለህዝብ በደረሱት 18 እና 19ኛ እትም የቴክ-ሳይንስ መፅሔቶቻችን ላይ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲውን በስፋት መቃኘታችን ይታወሳል፡፡ በሁለቱ ተከታታይ ፅሁፎች ዳሰሳ ከተደረገባቸው የፖሊሲው አቅጣጫና ስትራቴጂ፣ ትግበራ፣ አፈፃፀም እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች በተጨማሪ አሉበት የሚባሉ ክፍተቶችም በስፋት ተዳሰውበት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ክፍተቶች ውስጥ በዋናነት ፖሊሲው ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቶ ከማላመድ ባሻገር ለኢኖቬሽን የሚገባውን ትኩረት አለመስጠቱ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት ላይ በተገቢ መልኩ አለመስራቱ እንዲሁም የፖሊሲው ዕቅድ እና አተገባበር እርስ በእርስ መጣጣም አለመቻላቸው የይጠቀሳል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ይፈታል የተባለለት አዲሱ የፖሊሲ ረቂቅ “በ2040 ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ለኢትዮጵያ ብልጽግና ዋነኛ መሣሪያ ሆኖ ማየት” የሚል ርዕይን አስቀምጦ ሲነሳ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሰው ሃብት ልማት፣ አካባቢዊ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት፣ የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም አይ.ሲ.ቲ ልማት እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ጨምሮ በ12 ቁልፍ ናቸው ባላቸው ጉዳዮች ላይ ስትራቴጂዎችን የቀረፀ ነው፡፡

በዛሬው ምክክር ላይ ከገለፃው ባሻገር ከተጠሪ ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች በፖሊሲ ክለሳው ላይ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶች የተሰጡበት ውይይትን አድርገዋል፡፡Post Comments(0)

Leave a reply