...

የጸረ ወባ መድሃኒቶች የካንሰር ህክምና የጎንዮሽ ጉዳትን ለመቀነስ

የጸረ ወባ መድሃኒቶች በካንሰር ህክምና ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን መቀነስ የሚያችሉ ተስፋ ሰጭ ምክቶችን ማሳየታቸው ተነገረ፡፡ የመረጃ ምንጫችን የሆነው Technology.org ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲን ጠቅሶ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ በመደበኛነት ለወባ በሽታ ህክምና የሚውሉ የመድሃኒት አይነቶች የካንሰር ህሙማን የካንሰር መድሃኒቶችን ሲወስዱ ሊገጥማቸው ለሚችሉ የጤና እክሎች ለማስቀረት ያስችላሉ፡፡
በተለይ አቶቫኪዮን (Atovaquone) በመባል የሚታወቀው የጸረ ወባ መድሃኒት ከጉሮሮ እና ከኦክስጅን ጋር በተያያዘ ለሚመጣው lung tumour መሻሻል እንዳሳየ ተነግሯል፡፡ እንደሚታወቀው የካንሰር ህመም ከፍተኛ የሆነ የኦክስጅን መጠንን ይፈልጋል፡፡ ይህ ከፍኛ የሆነ የኦክስጅን ፍላጎት የተለያዩ ህዋሳትን በእጅጉ ይጎዳቸዋል፡፡ ለካንሰር ህክምና ከሚረዱ የተለያዩ ስልቶች መካከል ራዲዮ ቴራፒ አንዱ ሲሆን ይህ ስልት የካንሰር ህዋሳትን የሚያጠቃው ኦክስጅንን በመጠቀም ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ተስፋ ሰጭ መፍትሔዎች እየተገኙለት እንደሆነ ለሚነገረው ለካንሰር ህመም ህክምና አሁን ላይ የወባ በሽታን ለማከም በሰፊው እየተዘዋወረ ያለው መድሃኒት ሌላ አግዥ እንደሚሆን መረዳት ይቻላል፡፡
ምንጭ፡ Technology.org


Post Comments(0)

Leave a reply